ሆድና ህሊና
ጥንታዊ አባታችን—- ገና አዳም ሳየፈጠር፣
ይሄ ሁሉ ዘመን —- በሰው ላይ ሰቆጠር፤
ለምን ይሆን ከቶ —- የሚነሱን ጤና፣
ሙገት የመገጥሙን —- ሆደና ህሊና።
የዐለም ፈጥረታቶች —- ገዢ የሆነው ሰው፣
አስተወሎ መስሪያ —- ህሊና ሲሰጥው፤
ገና በጅምሩ —- በሆዱ ታለለና፣
ታናሽ ሆኖ ቀረ —- ተለቁ ህሊና።
የኽው እስከዛሬ —- ሆድ ባመጣው ጣጣ፣
ይኖራል የሰው ለጅ —- ከችግር ሳይወጣ፤
ታላቅ ቡርኩናውን —- ለታናሹ ሸጦ፣
አስተውይ ህሊና — በሆድ ተለወጦ።
እርገማን ሆኖብን —- ከአዳም የወረደ፣
በሰው ዘረያ ላይ —- እሳቱ ነደደ፤
ዳኛ በሌለብት —- እየተማዋገቱ፣
ሁድ አና ህሊና —- ስንቱን ሰው አሳቱ።
የማይቀርው መንገድ —- ያ ጉዞ ሳይመጣ፣
ከሆ መቆራኘት —- ምን አለብት ብንወጣ፤
እንደ ብዐሲት ሎጥ —- ድኒ ሳይወርደበን፣
ለህሊና ኖረን —- ምናለ ብንድን።
ከሰአት ና ዘመን የተወሰደ
ሻምበል ታደሰ ወ/ገብራኤል