ቁርኝት
የህይወት ጥሪ ነው መሰል፤
ላንገናኝ ያገናኘን፤
ላንሰናኝ ያሰናኝን፤
ላነቆራኝ ያቆራኘን፤
ባንድ ዘመን ተገናኘን።
የዘሆን ጆሮን ተመኝሁ፣ ሮርህን ተጠይፌ፤
በመደቤ ላይ ተቀምጠህ፣ በመርኩዝህ ተደግፌ፤
የአዞ እንባ ነው አልከኝ፣ የነፍሴን ለቅሶ ከደህ፤
ከማእድህ ተቓድሼ፣ ብታዛዬ ተጠልለህ።
የህይውት ጠሪ ነው መሰል፤
ላንገናኝ ያገናኘን፤
ላንሰናኝ ያሰናኝን፤
ላነቆራኝ ያቆራኘን፤
ባንድ ዘመን ተገናኘን።
መዝሙሬን እንደሃዘን ሙሾ፣ አላዘበኩኝ በእንባ፤
ደስታዬን ከደስታህ ላይሰምር፣ ወስጥህ ሰርጾ ልይገባ፤
የርቅ እጄን ብዘረጋ፣ ደስታህ ላያስፈግገኝ።
ምን አዚም ከኔ ጣድህ፣
ምኑ አዚም ከአንተ አዞረኝ።
ከፍካት ናፋቂዎች ይተወሰደ
በደሉ ዋቅጀራ